የምሥራች : የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና የተደረገላት ሕፃን ሁለተኛ የሕይወት ዕድል አገኘች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ባለው 5ኛው ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ዘመቻ፣ በአንደኛ የልደት ቀኗ የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና የተደረገላት የአንድ ዓመት ሕፃን አስደናቂ ታሪክ ትኩረት ስቧል።

ሕፃኗ ከአንድ ዓመት በፊት በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 6፡00 ሰዓት ላይ የተወለደች ሲሆን፣ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈጥሮ የልብ ክፍተት የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል።

የሕክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ ሕፃኗ ከተወለደችበት ጀምሮ በተፈጥሮ በነበራት የልብ ክፍተት ስትሰቃይ ቆይታለች። በአንደኛ ልደቷ ቀን የተከናወነው የቀዶ ሕክምና ግን ለሕፃኗ አዲስ የሕይወት ተስፋ እንደከፈተላት ተጠቁሟል።

የቀዶ ሕክምናውን ያከናወነው የታዝማ የልብ ቀዶ ሕክምና ቡድን በዘመቻው አካል ሆኖ ሕክምናውን የሰጠ ሲሆን፣ በተፈጥሮ የልብ ችግር ለሚሰቃዩ ሕፃናት ተስፋ እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።

የሕክምና ቡድኑ አባላትም ልዩ የሆነውን የልደት ቀን አጋጣሚ ከሕፃኗ ቤተሰቦች ጋር በሆስፒታሉ ውስጥ በማክበር ደስታቸውን ገልጸዋል።

ይህ አጋጣሚ የልብ ቀዶ ሕክምና በሕፃናት ሕይወት ላይ የሚያመጣውን ትልቅ ለውጥ የሚያሳይ ሲሆን፣ ለተመሳሳይ የጤና ችግር የሚሰቃዩ ቤተሰቦችም ተስፋ የሚሰጥ ተሞክሮ መሆኑ ተገልጿል።

#Ethiopia #Health #CardiacSurgery #PediatricHeartSurgery #DebreBirhan #HeartCare #MedicalMission #ChildHealth #Hope #Tazma #Getu





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: