የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በመስረቅ ያከማቸ ግለሰብ በ6 ዓመት እስራት ተቀጣየኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመስረቅ አከማችቶ የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በመስረቅ ያከማቸ ግለሰብ በ6 ዓመት እስራት ተቀጣ
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመስረቅ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በ6 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት አሰታውቋል፡፡
ግለሰቡ ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ አልሙኒየሞችና መዳቦች በመስረቅ ባሳለፍነው መጋቢት ወር መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ያሰታወሰው አግልግሎቱ፤ በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት ባደረገው ክርክር በግለሰቡ ላይ የ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲወሰን ማደረግ መቻሉን ለጣቢያችን የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተያያዘም በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ኬብሮን መድኃኒት ቤት አካባቢ በግንባታ ላይ ከሚገኝ ህንፃ ላይ የወደቀ ህንፃ መወጣጫ ዊንች በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብልና በትራንስፎርመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የገለጸው አገልግሎቱ፤ ተቋሙ ጉዳት የደረሰበትን የኤሌክትሪክ ኬብልና ትራንስፎርመር በመተካት ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከ1 ሚሊየን 9 መቶ ሺሕ ብር በላይ እንዲከፍል በፍርድ ቤት ስለመወሰኑ ገልጿል፡፡
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: