ጎግል ቅጣት ተከናነበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ቅጣቱ በአውሮፓ ሕብረት ታሪክ በቴክኖሎጂ ኩባንያ ላይ ከተጣሉ ግዙፍ ቅጣቶች መካከል አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።

የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጎግል በአንድሮይድ የሞባይል ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ አማካኝነት ተወዳዳሪዎቹን ገበያ እንዳይቀላቀሉ አግዷል በሚል የቀረበውን ክስ አጽድቋል።

በዚህም ጎግል የቀረበበትን የ4.1 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል አጸድቋል።

ፍርድ ቤቱ እ.ኤ.አ በ2018 ባደረገው ምርመራ ጎግል በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ጎግል ሰርች እና ክሮም ብሮውዘር እንዲጫኑ ግዴታ በመጣሉ የስማርት ስልክ አምራቾች አፕሊኬሽኖችን እንዳይጠቀሙ አድርጓል ሲል ከሷል።

ጎግል በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ ተደርጎበታል።

ጎግል ይህ ውሳኔ አንድሮይድ ክፍት እና ነጻ መድረክ እንዲሆን ያደረገውን ጥረት እንደማያገናዝብ ገልጾ ቅጣቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቃወም አስታውቋል።

ኩባንያው ከ2018 ጀምሮ ተገቢውን ማስተካከያ አድርጌያለሁ ቢልም ከቅጣት ማምለጥ ግን አልቻለም።

ይህ ውሳኔ የአውሮፓ ሕብረት የዲጂታል ገበያን (Digital Markets Act) ለመቆጣጠር እና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሞኖፖሊ አሰራር ለመግታት የሚያደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

​#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#EuropeanUnionhighercourt
#Google


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: