#Ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት “የታክስ አስተዳደር ለውጦች ፣ እድሎች፣ ተግዳሮቶችና ምርጥ ተሞክሮዎች” በሚል ርዕስ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የጋራ የውይይት መድረክ አዘጋጀ።
በመብትና ግዴታ ምንንነት ላይ ግንዛቤ ለማሳደግ እንዲሁም በመንግሥትና በንግዱ ዘርፍ መካከል ያለውን የመረጃ ክፍተት ለማጥበብ የሚያስችሉ ሃሳቦች በመድረኩ ተነስተዋል።
እንዲህ ያሉ መድረኮች የንግዱ ማኅበረሰቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ከመጠቆም ባለፈ ነጋዴው የፖሊሲ አውጪዎችን በሃሳብ እንዲሞግትና ተቋማዊ አሠራሮች የነጋዴውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንዲሻሻሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
በአሁኑ ወቅት የታክስ አስተዳደሩ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን በተለይም ወደ ዲጂታል የግብር አሰባሰብ ሥርዓት የተደረገው ሽግግር አልፎ አልፎ ከሚያጋጥሙ አነስተኛ የቴክኖሎጂ እክሎች በስተቀር በዘርፉ ላይ ለውጥ ማምጣቱ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ የግብር አሰባሰቡ ሂደት በከፍተኛ የታክስ መሸሸግ ችግር የተተበተበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በጥናት መሠረት 70 በመቶ የሚሆነው ታክስ ከፋይ ዓመታዊ ግብሩን አይከፍልም ተብሏል።
አንዳንድ የንግድ ተቋማት እስከ 10 ዓመት ድረስ ምንም ዓይነት ትርፍ እንዳላገኙና ዜሮ ሪፖርት ሲያቀርቡ መቆየታቸው ነው የተገለጸው።
ይህንን የግብር ስወራ ለመቅረፍና አሠራሩን ለማስተካከል በማሰብ መንግሥት በርካታ ለውጦችን እያደረገ ነው ተብሏል።
በአዲሱ የቴክኖሎጂ አሠራር አልፎ አልፎ የሲስተም መቆራረጥን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች ቢኖሩትም የግብር ከፋዩን እንግልት በመቀነስ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዚህም በተጨማሪ በግምት የሚተመነው ታክስ ነጋዴው ገና ወደ ሥራ ሳይገባ ከኪሱ የሚያወጣው ሳይሆን በመጀመሪያው የሩብ ዓመት የስራ ጊዜ ውስጥ ባከናወነው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተመሥርቶ የሚከፈል መሆኑ ተገልጿል። በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ታክስን በሚመለከት እንደየሁኔታው ከሁለት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የግብር ዕፎይታ እንደሚሰጥ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
📸 ከበደ መክብብ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen








No comments yet.