ሁለቱ ግለሰቦች ማማ ላይ ይዘውት የወጡት ጨርቅ ምን ተጽፎበታል?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአሜሪካ ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው ታዋቂው የኤምፓየር ስቴት ሕንጻ ጫፍ ላይ ሁለት ግለሰቦች በመውጣት መልዕክት የያዘ ጨርቅ መስቀላቸው ተሰማ።

ግለሰቦቹ ከምድር በላይ 1,454 ጫማ ከፍታ ላይ በሚገኘው የሕንጻው ማማ ላይ የሰቀሉት ጨርቅ “የፍቅር ኃይል የሥልጣንን ፍቅር ሲያሸንፍ ዓለም ሰላምን ይሆናል” የሚል ጥልቅ መልዕክት ያስተላልፋል።

እነዚህ ሁለት ሰዎች ይህንን ያህል ከፍታ ላይ በምን መንገድ ሊወጡ እንደቻሉ እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን የአካባቢው ፖሊስም ግለሰቦቹን ከማማው ላይ በሰላም ለማውረድ የተቻለውን አድርጓል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2