#Ethiopia | በእግርኳስ ዓለም ውስጥ ለቡድናቸው ያላቸውን ስሜት በተለየና በሚያስገርም መንገድ የሚገልጹ ደጋፊዎች አሉ። ነገር ግን እንደ ሚሼል ንኩካ ወይም በቅጽል ስሙ “ሉሙምባ ቪያ” ያለ ቁርጠኛ እና ልዩ ደጋፊ ማግኘት በላል አይሆንም!
ይህ ሰው በስታዲየም ውስጥ የሚፈጥረው ድባብ የስፖርቱ ዓለም ካያቸው እጅግ አስደናቂ ትዕይንቶች አንዱ ነው።
ሉሙምባ ቬያ ማነው? ለምንስ ልዩ ሆነ?
ይህ ደጋፊ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በሚያደርግበት ጊዜ ጨዋታው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ለ90 ደቂቃ ሙሉ ሳያንቀሳቅስ ልክ እንደ ሐውልት ቆሞ ጨዋታውን ይታደማል።
”ሉሙምባ ቬያ” የኮንጎን ታዋቂ የነጻነት ታጋይ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባን በመልክ በመምሰል ነው።
እግርኳስን ከሀገር ታሪክ ጋር በማሰናሰል የኮንጎን ገጽታ በዓለም አቀፍ መድረክ እያስተዋወቀ ይገኛል። እስከ 2026ቱ የዓለም ዋንጫ ጉዞ ድረስ የኮንጎ ብሔራዊ ቡድን በሄደበት ሁሉ ትልቅ ትኩረትን እየሳበ የሚገኝ እውነተኛ ደጋፊ ነው።
አንዳንዶች እግርኳስ ስፖርታዊ ጨዋታ ብቻ ሊሆን ይችላል ለሉሙምባ ቬያ ግን ሀገራዊ ማንነትን ታሪክንና ፍቅርን ለዓለም የሚያሳይበት ትልቅ የጥበብ መድረክ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.