የአለማችን ውዱ ደብዳቤ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከ170 ዓመታት በፊት አንድ የወይን ነጋዴ ፈረንሳይ ለሚገኙ አጋሮቹ የላከው እጅግ አሰልቺ የተባለው ደብዳቤ በዓለም ላይ በጣም ውድ የሆነው የፖስታ ሰነድ ሆኖ በጨረታ ተሽጧል።

በደብዳቤው ላይ የሰፈረው ቃል እንዲህ የሚል ነበር።

“የላካችሁልን 30 በርሜል ወይን ደርሶናል” የሚል በጣም ቀላል መልዕክት ያዘለ ነበር።

ነገር ግን ይህ ደብዳቤ ውድ የሆነበት ዋናኛ ምክንያት የውስጡ ይዘት ሳይሆን ከውጭ የተለጠፉት ሁለት የፖስታ ቴምብሮች ናቸው።

እነዚህ ቴምብሮች በእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ወቅት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተሙ በመሆናቸውና ዛሬ በዓለም ላይ ጥቂት ብቻ የቀሩ ብርቅዬ ንብረቶች ተደርገው በመቆጠራቸው የተነሳ ነው።

ይህ ደብዳቤ ነው በእንግሊዝ ጨረታ ቀርቦ 4 ሚሊዮን ፓውንድ የተሸጠው።

አንዳንድ ጊዜ ምንም የሌለው የሚመስል ቀላል ነገር በታሪክ አጋጣሚ ምን ያህል ውድ ሊሆን እንደሚችል ይህ ደብዳቤ ትልቅ ማሳያ ነው ሲል የፃፈው ኦዲቲ ሴንትራል ነው።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Audditycentralnews
#WorldExpensiveLetter


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2