ለስድስት ቀናት ተቀብሮ የነበረ ሕፃን በሕይወት ተረፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቬንዙዌላ በተከሰተው አስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በፈራረሱ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ውስጥ ለስድስት ቀናት ተቀብሮ የነበረ አንድ የሦስት ዓመት ሕፃን በሕይወት ተገኝቶ ተረፈ።

ክሊበር ሞራን (Klieber Moran) የተባለው ይህ ሕፃን የተገኘው በሰሜናዊ ላ ጉዋይራ (La Guaira) ግዛት በሚገኝ የአፓርታማ ፍርስራሽ ውስጥ ሲሆን፣ የጆርዳን የነፍስ አድን ቡድን አባላት በካሜራ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሊያወጡት ችለዋል።

የሕፃኑ መተርፍ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተስፋን የፈጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በካራካስ በሚገኝ የሕክምና ማዕከል ተወስዶ እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

ሰኔ 24 ቀን 2026 ዓ.ም. ቬንዙዌላን በአንድ ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ያናወጧት ሁለት እጅግ ኃይለኛ (7.2 እና 7.5 በሬክተር ስኬል) የመሬት መንቀጥቀጦች ነበሩ።

እስካሁን በተረጋገጠው መረጃ መሠረት የሟቾች ቁጥር 1,943 የደረሰ ሲሆን፣ ከ 10,500 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) እንደገለጸው እስካሁን ድረስ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ያሉበት አልታወቀም።

የናሳ (NASA) የሳተላይት መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአደጋው ሳቢያ በመላው ሀገሪቱ 60,000 የሚጠጉ ሕንጻዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወድመዋል።

አደጋው ከተከሰተ ስድስት ቀናት ያለፉ በመሆኑና ወሳኙ የ72 ሰዓታት የነፍስ አድን መስኮት በመዘጋቱ፣ አሁን ላይ ፍለጋው አስከሬኖችን የማውጣት አሳዛኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪም በሕይወት የተረፉት ዜጎች ከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ፦

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንደገለጸው በመላው ሀገሪቱ 38 ሆስፒታሎች የተጎዱ ሲሆን የሕክምና ሥርዓቱ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቋል።

የመጠለያ፣ የንጹህ ውሃና የንፅህና መጠበቂያዎች እጥረት እንደ ጉፍኝት (Measles)፣ ዴንጊ እና ወባ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዲቀሰቀሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገልጿል።

በተለይ በላ ጉዋይራ ግዛት መሰረታዊ አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን፣ ዜጎች ለምግብ እርዳታ ረጅም ሰልፎችን በመያዝ ላይ ናቸው።

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) 47 ቶን የሚመዝን የሕክምናና የአደጋ ጊዜ ቁሳቁስ ያደረሰ ሲሆን፣ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮ፣ እስራኤልና ከሌሎችም ሀገራት የተላኩ የነፍስ አድን ቡድኖች በቦታው ይገኛሉ።

የአካባቢው ነዋሪዎች የመንግሥትን የዕርዳታ አሰጣጥ ፍጥነት እየተቹ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ ዘመዶቻቸውን ለማግኘት በፍርስራሹ ላይ በባዶ እጃቸውና በባህላዊ መሣሪያዎች የሚቆፍሩ ዜጎች ቁጥር በርካታ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1