#Ethiopia | የቀድሞው የሶቪየት ሕብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን የበኩር ልጅ ያኮቭ ድዙጋሽቪሊ ከአባቱ ጋር በነበረው እጅግ የሻከረ ግንኙነት ምክንያት ለከፍተኛ ስሜታዊ ጫና ተዳርጎ እንደነበር ይነገራል።
ያኮቭ ካልተሳካ ትዳር እና ለዓመታት ከዘለቀ የስነ-ልቦና ቀውስ በኋላ በ1920ዎቹ ዕድሜው ላይ ደረቱ ላይ በመተኮስ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል። በርካታ የታሪክ ተመራማሪዎች ለዚህ የራሱን ሕይወት ለማጥፋት የዳረገው አስከፊ ሙከራና ለደረሰበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም ከአባቱ ከስታሊን ጋር የነበረው አስቸጋሪ ግንኙነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ያምናሉ።
ስታሊን ለልጁ የራስ ማጥፋት ሙከራ የሰጠው ምላሽ ነው ተብሎ የሚነገረውና “ቀጥ አድርጎ መተኮስ እንኳን አይችልም” የሚለው ዝነኛ አባባል በተለያዩ የሕይወት ታሪክ መጻሕፍትና ማስታወሻዎች ውስጥ ተጠቅሷል።
የያኮቭ አሳዛኝ የሕይወት ታሪክ ይበልጥ የከፋ መልክ የያዘው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ኃይሎች እጅ በተማረከበት ጊዜ ነው። ጀርመኖች ያኮቭን በከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚገኝ የጀርመን የጦር ምርኮኛ ለመለወጥ ያቀረቡትን የምርኮ ልውውጥ ጥያቄ ስታሊን “ጄኔራልን በልጅ አልለውጥም” በማለት ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።
በመጨረሻም ያኮቭ በ1943 በጀርመን የጦር ምርኮኞች ካምፕ ውስጥ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን ይህም የጦርነቱ ሰለባ ከሆኑት በርካታ ወገኖች መካከል አንዱ አድርጎታል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.