በቻይና የሙቀትን ለመቋቋም የዘረጋችው የውሃ ማፍሰስ ቴክኖሎጂ መነጋገሪያ ሆኗል!በአውሮፓና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አስከፊ የሙ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በቻይና የሙቀትን ለመቋቋም የዘረጋችው የውሃ ማፍሰስ ቴክኖሎጂ መነጋገሪያ ሆኗል!
በአውሮፓና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አስከፊ የሙቀት ማዕበል በተከሰተበት በዚህ ወቅት፣ በቻይና የመኖሪያ መንደሮች ውስጥ የተዘረጉ አስደናቂ ከቤት ውጪ ማቀዝቀዣ ሥርዓቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ ይገኛሉ።
በተለይም ሰፊ የመኖሪያ ሕንፃዎች ግቢዎችን፣ መናፈሻዎችንና የእግር መንገድ ቦታዎችን ለማቀዝቀዝ የተዘረጉት የውሃ ማፍሰስ ሥርዓቶች ትልቅ መነጋገሪያ ሆነዋል።
ምዕራባውያን አገራት ከሙቀት ማዕበል ጋር እየታገሉ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ይህ ቴክኖሎጂ የቻይናን ዘመናዊና ፈጣን የሕዝብ መሠረተ-ልማት አቅም የሚያሳይ ነው በሚል በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን እያተረፈ ነው።
የዚህ ቴክኖሎጂ መሠረታዊ ሳይንስ ፈሳሽን ወደ ትነት የመቀየር ሂደት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ ይህም ልክ የሰውነታችን ላብ በሚተንበት ጊዜ ቆዳችንን እንደሚያቀዘቅዝልን ዓይነት ተፈጥሯዊ ሳይንስ ነው።
ሥርዓቱ ከፍተኛ ግፊት ያላቸው ፓምፖችንና ልዩ ማፋሰሻዎችን በመጠቀም በጣም ጥቃቅን የውሃ ጠብታዎችን ወደ አየር ይረጫል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: