#Ethiopia | የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአሐዱ፡ባንክ ጉዞ ውስጥ ጎልህ ስፍራ የሚሰጠው የስኬት ምዕራፍ ነው።
በዚህም መሰረት፦
ከመጠባበቂያና ግብር በፊት አምና ካስመዘገበው ጠቅላላ ትርፍ የ94.2% ዕድገት በማስመዝገብ ብር 1.15 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል፤
የባንኩ ጠቅላላ ገቢም ወደ ብር 3.2 ቢሊዮን ከፍ ያለ ሲሆን፤ ይህም የ52% ዕድገት አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ወደ ብር 10.5 ቢሊዮን ከፍ በማለት የ32% ዕድገትን አሳይቷል።
ባንኩ የ126 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በበጀት ዓመቱ ያገኘ ሲሆን፤ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ58% ዕድገት ያመለክታል።
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከብር 10.05 ቢሊዮን ወደ ብር 14.21 ቢሊዮን ያደገ ሲሆን፤ ይህም የ41.39% ዕድገት የታየበት ነው።
ባንኩ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 1.34 ሚሊዮን በማሳደግ መሰረቱን እያሰፋ ይገኛል፤ አሐዱ፡ባንክ በዋና ዋና መለኪያዎች የላቀ የፋይናንስ ዕድገት ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን፤ የባንኩን የወደፊት ትልም የሚያሳይ 2ቢ+ጂ+15 (2 ምድር ቤት + ምድር ወለል + 15) ፎቅ ታላቅ ህንጻ ባለቤት በመሆን እና ሁነኛ የዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (አሐዱ ሌሉ እና ማይድረስ) አበልጽጎ ለአገልግሎት ማዋል መቻሉ የበጀት ዓመቱ ተጨማሪ አንጸባራቂ ስኬቶች ናቸው።
በአጠቃላይ፤ አሐዱ፡ባንክ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 የተጠናቀቀውን የ2025/26 በጀት ዓመት በአንጸባራቂ ስኬቶች ታጅቦ ማጠናቀቁን ማወቅ ተችሏል።
ከብዙዎች ለብዙዎች
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.