‎የ70 እና የየ80 ዎቹ ወርቃማው የሙዚቃ ዘመን በሜላት ቀለመወርቅ ይደገም ይሆን?

- Advertisement -
Sidebar AD


‎ድምፃዊቷ በማህበራዊ ሚዲያ እንደ ገለፀችው
‎ ከጥላሁን ገሰሰ እስከ ማህሙድ አህመድ ከአስቴር አወቀ እስከ እጅጋየሁ ሽባባው /ጂጂ/ ከአልበም ስራ እስከ መድረክ እጀባ ዘመን የማይሽራቸው ስራዎችን በመስራት ስማቸው የሚጠራ ሀገራችን አሉኝ የምትላቸው ድንቅ ሙዚቀኞች ከሆኑት አበጋዝ ክብረወርቅ ሽወታ: ሄኖክ ተመስገን : ያሬድ ተፈራ : ግሩም መዝሙር : ዘሪሁን በለጠ : ሳሚ ጅፋር እንዲሁም ወጣቱ ሄኖክ ድለቃ በሙሉ ባንድ ሙዚቃውን የተጠበቡበት መሆኑን ገልፃ የእሷንም ብቃት እንዳሳየችበት ገልፃለች ።

‎ይህ ድንቅ ሙዚቀኞች የተሰባሰቡበት እና እንደ 70ዎቹን እና የ80ዎቹ በሙሉ ባንድ በመድረክ ላይ የተቀዳ ሙዚቃ ለመስራት እና ሙዚቀኞችን ለማሰባሰብ ብዙ ግዜ እንደ ወሰደ የተናገረች ሲሆን ምንም አድካሚ ቢሆንም ለአድማጩ የሚመጥን ምርጥ ስራ ነገ አርብ ይዤ እመጣለሁ ብላለች ።

‎ያ በኢትዮጵያ መዚቃ ታሪክ ወርቃማ ነው የተባለለትን ብቃት ያላቸው ሙዚቀኞች እና ድምፃዊያን ተገናኝተው በሙሉ ባንድ እየተሰራ ዘመን ተሻጋሪ የሆነው ሙዚቃ በወጣቷ ድምፃዊት ሜላት ቀለመወርቅ ሲደገም እናየው ይሆን? ሙዚቃስ ከአንድ የስቱዲዮ ኪቦርድ ስራ ወጥቶ በሙሉ ባንድ ከነክብሩ ተሰርቶ እንሰማው ይሆን? ሜላት ቀለመወርቅስ ልክ እንደ አስቴር አወቀና ሀመልማል አባተ በመድረክ ላይ ብቃቷን ታስመሰክር ይሆን? ለሁሉም ጥያቄ አርብ 8:00 በራሷ ዩቱዩብ ቻናል ላይ የሚለቀቀው “መላ መላ” የተሰኘው ስራ መልስ የሚሰጠን ይሆናል ።

ጋዜጠኛ መሉቀን አስን


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: