ቴክኖ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ቱሪዝም በሞባይል ፎቶግራፍ ለማስተዋወቅ የ10 ቀናት የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ቴክኖ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህቦች በሞባይል ፎቶግራፍ ጥበብ ለማስተዋወቅ ያለመ የ10 ቀናት የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን እና የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል። ኩባንያው ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽን፣ የሀገሪቱን የተፈጥሮ ውበት፣ ታሪካዊ ቅርሶች እና ባህላዊ እሴቶች የሚያሳዩ ከ100 በላይ በሞባይል ስልክ የተነሱ ድንቅ ፎቶግራፎችን ለዕይታ አብቅቷል።

​በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው የዚሁ ኤግዚቢሽን የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ቴክኖ ኢትዮጵያ ይህንን ዝግጅት ያዘጋጀው ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ ከቦርድ ሴልፎን አዲስ አበባ እንዲሁም ከህፃናትና ወጣቶች ቲያትርና ሲኒማ አዳራሽ ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል።

​በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡት ምስሎች በሙሉ በኩባንያው የቅርብ ጊዜ ምርት በሆነው “TECNO CAMON 50 Pro” ስማርት ስልክ ብቻ የተነሱ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የሞባይል ስልኩን የፎቶግራፍ ጥራትና የቴክኖሎጂ ደረጃ ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል። ስልኩ 50 ሜጋ ፒክስል (50MP) የካሜራ ሲስተም እና AI ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ እንደሆነም ተጠቁሟል።

​የዚህ መርሃ ግብር ዋነኛ አካል የሆነው በቴክኖ ኢትዮጵያ፣ በአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ በቪዚት አዲስ አበባ እና በህፃናትና ወጣቶች ቲያትርና ሲኒማ መካከል በጋራ ለመስራት ተስማምቷል። ይህ ስምምነት የቴክኖሎጂ፣ የፎቶግራፍ እና የፈጠራ ስራዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ በጋራ ለማስተዋወቅ ያለመ እንደሆነ ስምምነቱን የፈረሙት አካላት አስታውቀዋል።
#ሳይ_ቴክ






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2