ነፃ የሥራ ዕድል በጣሊያን፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቅጥር ምዝገባ ጀመረ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጣሊያን መንግስት ጋር ባደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በሆቴልና መስተንግዶ ዘርፍ ለሚገኙ ልዩ ልዩ ክፍት የሥራ መደቦች የቅጥር ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ።
ይህ ህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም የዜጎችን መብትና ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ የሚከናወን ሲሆን፣ ለምዝገባውም ሆነ ለሂደቱ ምንም ዓይነት ክፍያ እንደማይጠየቅ ሚኒስቴሩ አፅንዖት ሰጥቷል።
በአጠቃላይ ለ72 ክፍት የሥራ ቦታዎች የወጣው ይህ ጥሪ የሚከተሉትን መደቦች ያካትታል፦
የቢሮና መስተንግዶ ሠራተኞች፦ 19 ጸሐፊዎች፣ 20 የሆቴል ፅዳት ሠራተኞች እና 4 የቢሮ አስተናጋጆች።
የወጥ ቤትና የፅዳት ባለሙያዎች፦ 13 ረዳት ሼፎች፣ 11 ዕቃ አጣቢዎች እና 3 የወለል ረዳቶች።
ቴክኒክና እንክብካቤ፦ 1 የጥገና ቴክኒሺያን እና 1 የስፓ/ማሳጅ ቴራፒስት።
አብዛኛዎቹ የሥራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አመልካቾች ተዛማጅ የሥራ ልምድ እና የእንግሊዝኛ ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል።
ለመመዝገብ የሠራተኛ መለያ ቁጥር (Labor ID) መያዝ ግዴታ ነው። ፍላጎት ያላቸው ዜጎች በ lmis.gov.et ድረ-ገጽ በመመዝገብና በአቅራቢያቸው በሚገኝ ወረዳ ባዮሜትሪክስ በመስጠት መለያ ቁጥሩን ማውጣት ይችላሉ። በመቀጠልም በይፋዊው የማመልከቻ ሊንክ (https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/) በመጠቀም በነፃ ማመልከት ይኖርባቸዋል።
ሚኒስቴሩ ለምዝገባው ለማንም አካል ውክልና አለመስጠቱን ገልጾ፣ ዜጎች ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

No comments yet.