ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነውበኢትዮጵያ ድንበር ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነውየሱዳን ጦር ኃይል  በደቡብ ምስራቅ ብሉ ናይል (ሰማያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️
በኢትዮጵያ ድንበር ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው‼️
የሱዳን ጦር ኃይል  በደቡብ ምስራቅ ብሉ ናይል (ሰማያዊ አባይ) ግዛት የምትገኘውን እና ከኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ጋር የምታዋስነውን ስልታዊ የድንበር ከተማ ኩርሙክን መልሶ ለመቆጣጠር ከትናንት አንስቶ ሰፊ ማጥቃት መክፈቱን አናዶሉ የጦር ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ይህ ጥቃት የተሰነዘረው ከአማጺው የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና ከሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ጋር ከባድ ውጊያ ከተደረገ በኋላ ነው።
የዜና ጣብያው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉትን የጦር ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የሱዳን ጦር ኃይል እና አጋሮቹ በኩርሙክ ከተማ ዳርቻ በሚገኙት የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) የፊት መስመር ይዞታዎች ላይ ለሰዓታት ከቆየ ውጊያ በኋላ ከባድ ጥቃት ሰንዝረዋል።
ይህ ጥቃት ከተማዋን መልሶ ለመቆጣጠር ያለመ የኦፕሬሽን አካል ሲሆን፣ ከተማዋ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ በRSF እና በሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ጥምረት ቁጥጥር ስር ቆይታለች።
የመጨረሻው ጥቃት የተሰነዘረው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሚደገፈው የፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና አጋር ሚሊሻው የሱዳን ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) የዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ ኩርሙክን ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ በብሉ ናይል ክልል ውስጥ ለወራት የቆየው ወታደራዊ ዘመቻ በበረታበት ወቅት ነው።
ይህ ሁኔታ ግጭቱ ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ሊሻገር ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1