የተረሳው የዜጎች እልቂት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቬኒዙዌላ ከሳምታት በፊት በተከሰቱት ሁለት ተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ሳብያ የሟቾች ቁጥር ወደ 2,645 አሻቅቧል።

በአደጋው 12,600 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ አሁንም የት እንዳሉ አልታወቀም።

በአደጋው ከ58,000 በላይ ህንፃዎች ሙሉ በሙሉ የፈረሱ ሲሆን ላ ጉዋይራ የተሰኘችው ከተማ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዷ መሆኗ ታውቋል።

እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 6,462 ሰዎች በህይወት መትረፋቸው የአካባቢው ሀላፊዎች ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚገኙ የነፍስ አድን ቡድኖች አሁንም ስራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ነው የተነገረው።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን ተከትሎ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።

የዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ሰለባ ለሆኑ ዜጎች የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሚገኙ መረጃዎች አመላክተዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Venezuelaearthquakes
#ShafaqNewsCaracas


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1