#Ethiopia | አዳዲስ የፈጠራ ቢዝነሶች (ስታርትአፖች) በምን ምክንያት ከገበያ እንደሚወጡ እና ለውድቀት እንደሚዳረጉ የሚያሳይ አዲስ የጥናት ውጤት ይፋ ተደርጓል።
‘ፋውንድድሲኢኦ’ የተባለ ተቋም በየካቲት ወር 2026 ባወጣው ሰፊ የዴታ ትንተና ዘገባ እንደ እንደ ውጭዎቹ አቆጣጠር ከ2015 እስከ 2026 ባሉት ዓመታት ውስጥ የተዘጉ እና የከሸፉ ከሦስት ሺህ በላይ ስታርትአፖችን መረጃ በመመርመር ተቋማቱን ለውድቀት የዳረጓቸውን ዋነኛ ምክንያቶች በዝርዝር አስቀምጧል።
በጥናቱ ውጤት መሠረት 44 በመቶ የሚሆኑት አዳዲስ ቢዝነሶች የሚከሽፉት ለሚያቀርቡት ምርት ወይም አገልግሎት በቂ የገበያ ፍላጎት ስለማይኖር መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ በመቀጠል የገንዘብ እጥረት ማጋጠም ወይም የሥራ ማስኬጃ በጀት ማግኘት አለመቻል 31 በመቶ ድርሻ በመያዝ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በተጨማሪም ትክክለኛውን የሥራ ከባቢ(ባልደረባ) አለመምረጥ ወይም በመሥራቾች መካከል የሚፈጠር አለመግባባት በሌሎች ተፎካካሪ ድርጅቶች ከገበያ መገፋት እንዲሁም የተጋነነ የዋጋ እና የወጪ አስተዳደር ችግሮች ቢዝነሶቹን ለፈጣን ውድቀት ከሚዳርጉ ቀዳሚ አምስት ምክንያቶች መካከል በዋናነት ተጠቅሰዋል።
ይህ ትንተና በግልጽ እንደሚያሳየው አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን ይዞ ወደ ገበያ መቀላቀል ብቻውን ስኬትን እንዳልሆነና የገበያን ትክክለኛ ፍላጎት አስቀድሞ አለማጥናት የፋይናንስ አቅምን በአግባቡ አለመመጠን እንዲሁም ጠንካራ የሥራ ቡድን አለመፍጠር አብዛኛዎቹን ጀማሪ ተቋማት ገና በጅምራቸው እንዲቀጩ እያደረጋቸው ይገኛል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.