ፑቲን ለባላንጣቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ 250ኛ ዓመት የነፃነት በዓሏን በምታከብርበት ታሪካዊ ዕለት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ልከዋል። ፕሬዝዳንቱ በመልእክታቸው የአሜሪካ የነፃነት አዋጅ መፈረም የሀገሪቱን መወለድ ከማብሰር ባለፈ በዓለም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታሪካዊ ክስተት መሆኑን አውስተዋል።

​ሩሲያ በወቅቱ ከእንግሊዝ አገዛዝ ለመላቀቅ ለሚታገሉት የሰሜን አሜሪካ ቅኝ ግዥዎች የማያወላውል ድጋፍ ስታደርግ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዝዳንት ፑቲን ባለፉት ሁለት ተኩል ምዕተ ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል በርካታ ታሪካዊ ግንኙነቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ወቅት በአጋርነት በመሰለፍ የሰው ልጅን ከናዚዝም አሰቃቂ ድርጊቶች በጋራ ነፃ እንዳወጡና ለዘመናዊው የዓለም ሥርዓት መመሥረትም ወሳኝ ሚና መጫወታቸውን አብራርተዋል።

​በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ግዙፍ የኒውክሌር ኃይል ባለቤቶች የሆኑት ሩሲያና አሜሪካ ዓለም አቀፍ ሰላምና መረጋጋትን የማስጠበቅ ልዩ ኃላፊነት እንዳለባቸው ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል የሚገነባው ገንቢ ፍትሐዊና የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገ ግንኙነት ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጥቅም እንደሚውል ያላቸውን ጠንካራ እምነት አክለው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የአሜሪካ ዜጎች የጤና፣ የደስታና የብልጽግና ምኞታቸውን በማስተላለፍ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

ሠላማችን ይብዛ!!!

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: