የአውሮፓ አባል ሀገራት ለዩክሬን 80 ቢሊዮን ዶላር የጦር ድጋፍ ሊያደርጉ ነው።
#Ethiopia | ሀገራቱ በየዓመቱ 70 ቢሊዮን ዩሮ (ወደ 80 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ) ወታደራዊ ድጋፍ ሊያደርጉ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ድጋፍ ለሁለት ዓመታት (2026 እና 2027) የሚቀጥል ይሆናል ነው የተባለው።
ይህ ድጋፍ ዩክሬን እስከ 2027 መጨረሻ ድረስ ወታደራዊ አቅሟን እንድታሳድግ ለማስቻል ያለመ ነው ።
የተመደበው 80 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የተመደበ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል በአውሮፓ ህብረት የተፈቀደው የብድር ድጋፍ እና የአባል ሀገራት የሁለትዮሽ የጦር መሳሪያ ድጋፎችን ያካተተ ነው።
በሐምሌ 7 እና 8 በአንካራ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ሩሲያ ለአውሮፓ እና አትላንቲክ ቀጠና ደህንነት ስጋት መሆኗ በይፋ ያውጃሉ ተብሏል።
ይህ ስምምነት በተለይ የአሜሪካ የፖለቲካ አቅጣጫዎች በሚቀያየሩበት ወቅት መደረጉ አውሮፓውያን ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍ በራሳቸው አቅም የመምራት ፍላጎት እንዳላቸው አቅማቸውን የሚያሳዩበት ይሆናል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nato #Ankara #Ukraine
#AnnualsupportUkraine
Source: GetuTemesgen









No comments yet.