#Ethiopia | የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,931 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።
የትምህርት ገበታቸውን በስኬት አጠናቀው ለምረቃ ከበቁት የዘንድሮ ተመራቂዎች መካከል 849ኙ ሴቶች መሆናቸው
በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲውን በዘንድሮ አመት 1,864 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 45 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ጨምሮ 939 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ ውስጥ 45 ተማሪዎች በሦስተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ሲሆኑ 83 የሚሆኑት ደግሞ በስፔሻሊቲ አጠናቀዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፋና ሓጎስ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማረጋገጥ እና የተመራቂዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ሰፊ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ መደረጉን ጠቁመው፣ ተመራቂዎቹ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ኅብረተሰቡን በቅንነትና በትጋት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#MekelleUniversity #Graduation#EthiopianUniversities#HigherEducation



Source: GetuTemesgen









No comments yet.