#Ethiopia | ታዋቂው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ንብረቱንና ሁሉንም ነገር ላጣው አንድ ቬኔዝዌላዊ ታዳጊ ያደረገው ሰብዓዊ ተግባር የበርካቶችን አስደስቷል።
አንድሬስ የተባለው ይህ ታዳጊ ከአደጋው በኋላ ያስተላለፈውን አሳዛኝ መልእክት የተመለከተው ሮናልዶ የልጁን ስሜት በመጋራት አፋጣኝ ምላሽ ሰጥቷል።
ተጫዋቹ ለታዳጊው የማጽናኛና የብርታት ቃላትን ከመላክም ባሻገር “ከምጫወትባቸው ጨዋታዎች በአንዱ ላይ መጥተህ እንድትታደም እፈልጋለሁ” በማለት በአካል ተገኝቶ ጨዋታውን እንዲመለከት ልዩ ግብዣ አቅርቦለታል።
ይህ የሮናልዶ አርአያነት ያለው ተግባር በክፉው ጊዜ ውስጥ ለሚገኝው ታዳጊ አንድሬስም ትልቅ ጥንካሬንና ብሩህ ተስፋን የቸረ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.