የባሕር በር ለማግኘት በሚደረገው ጉዞ የጦር መኮንኖች ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኋል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላኢትዮጵ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የባሕር በር ለማግኘት በሚደረገው ጉዞ የጦር መኮንኖች ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኋል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ‼️
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት በምታደርገው ጉዞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኋል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በስትራቴጂና ደኅንነት ጥናት ዘርፍ የላቀ ብቃት ያላቸውን 42 ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና ከሲቪል ደኅንነት ተቋማት የተውጣጡ መሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጉዞ ፈታኝ መስመሮችን ማለፍ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ተመራቂዎች ወደ ስራ ስትሰማሩ በትምህርት ቆይታችሁ የቀሰማችሁትን እውቀትና ክህሎት በተግባር ከሚገጥሟችሁ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ ለውጡ በግልፅ የሚታይ የአመራር ስራ መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ተደምጠዋል።
ሰራዊቱ ወሳኝ የዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህ ሂደት የላቀ አስተዋፅኦ ለማበርከት በከፍተኛ ተነሳሽነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1