#Ethiopia | ሁነቱ የተከፈተው ቴክኖ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር አብረው ለመስራት በተስማሙበት መድረክ ነው።
የሀገርን ገፅታ ለመገንባትና የቱሪዝም መዳረሻዎችን በቴክኖሎጂ የታገዘ የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልታዊ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈርሟል።
ስምምነቱ የተፈረመው ቴክኖ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከቦርድ ሴል ፎን አዲስ አበባ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው 3ኛው ዙር የፎቶ ኤግዚቢሽን መክፈቻ ላይ ነው።
በሕፃናትና ወጣቶች ትያትር ኮምፕሌክስ በይፋ በተከፈተው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ቴክኖ ኢትዮጵያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውል ተፈራርመዋል።
ይህም ሁለቱ ተቋማት በቱሪዝም እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በቅንጅት በመስራት፣ የሀገር ውስጥ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ማህበረሰቡ የሀገሩን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ እሴቶች እንዲያውቅ ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ አዳዲስ የካሜራ እና የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ ወይም AI ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተነሱ ከ100 በላይ ልዩ ልዩ የፎቶግራፍ ስራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።
ቴክኖሎጂን ለሀገር ገፅታ ግንባታና ለኪነጥበብ እድገት ማዋል ላይ ትኩረት ያደረገው ይህ የፎቶ ኤግዚቢሽን፣ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፤ ከ10 ሺህ በላይ ታዳሚዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
ድርጊቱ በዘርፉ ላሉ ባለሙያዎችና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው አዲስ መነቃቃትን እንደሚፈጥርም ተነግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Addisababaturism #tecnoethiopia



Source: GetuTemesgen








No comments yet.