ያልተመዘገቡ ዲጂታል ሚዲያዎችን ወደ ሕጋዊ መስመር የሚያመጣ የአዋጅ ማሻሻያ ሊደረግ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አሁን ላይ በበይነ መረብ (ዲጂታል) ሚዲያው ዘርፍ የሚታየውን የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት ለመግታት፣ ያልተመዘገቡ ሚዲያዎችን ወደ ሕጋዊ የምዝገባ ሥርዓት የሚያስገባ የአዋጅ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።

‎የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ ይህንን የገለጹት፣ “ብቃት ያለው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ የሚዲያ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

‎ዳይሬክተሯ በዚሁ ጊዜ እንዳብራሩት፣ ከአመታት በኋላ በሚዲያው ዘርፍ የተደረገውን ሰፊ ሪፎርም ተከትሎ ድረ-ገጾችን የማፈንና የመዝጋት አሰራር በመቅረቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ጠንካራና ሚዛናዊ የዲጂታል ሚዲያዎች ሊፈጠሩ ችለዋል።

‎​ይሁን እንጂ ይህንን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው የሕዝብን አመኔታ ካገኙት ባሻገር፣ የተወሰኑት የዲጅታል ሚዲያዎች የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ እንዲሁም የሀገርን ሉዓላዊነትና የጋራ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት መበራከታቸውን ዳይሬክተሯ በንግግራቸው አብራርተዋል።

‎ይህንን አሳሳቢ ተግዳሮት ለመቅረፍም ባለሥልጣኑ በርካታ ተከታዮች እያሏቸው ነገር ግን ሳይመዘገቡ በዘፈቀደ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎችን ሕጋዊ ለማድረግ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎አዲሱ አሰራር በፓርላማ ጸድቆ ሲተገበርም፣ ማንኛውም ዲጂታል ሚዲያ በሕጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ ገብቶ ለሀገር ሰላምና ለብሔራዊ ጥቅም በኃላፊነት ስሜት መሥራት እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

‎​የባለሥልጣኑ ዋና ዓላማ ተቋማትን መቅጣት፣ መዝጋት ወይም መቆጣጠር ብቻ አለመሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ኃይማኖት፣ ተቋሙ ከቁጥጥር ይልቅ በአቅም ግንባታ፣ በምክክር እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል።

‎በመሆኑም ሕጋዊ ሆነው ለሚመዘገቡ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች የጋዜጠኝነት መታወቂያ ከመስጠት ጀምሮ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን የሚያካትቱ የማበረታቻ ሥርዓቶች እንደሚዘረጉ ተናግረዋል።

‎በመጨረሻም የዘርፉ ባለሙያዎች እርስ በርስ የሚተራረሙበት፣ ለሙያዊ ሥነ-ምግባር መከበር የሚቆምና በሌሎች ሀገራት እንደሚታየው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል ጠንካራ የጋዜጠኞች ማኅበር በማቋቋም በጋራ እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

‎በጌትነት ተመስገን
📷 ኢመብባ
‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ

‎#Ethiopia #EthiopianMedia #DigitalMedia #Journalism #MediaRegulation #EthiopiaNews






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2