አንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች!

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በዘመን አይሽሬ (Oldies) እና በባህላዊ ስራዎቿ የብዙዎችን ልብ የማረከችው አንጋፋዋ ድምፃዊትና የዜማ ደራሲ ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰምቷል።

የማይረሱ ስራዎቿ፦
“አራዳ”፣ “ምኒልክ”፣ “ይዳኘኝ ሰው” እና በርካታ ስራዎቿን ለህዝብ ያበረከተች ድንቅ አርቲስት ነበረች።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከዓለማዊ ሙዚቃ ርቃ፣ ህይወቷን ሙሉ በሙሉ ለመንፈሳዊ አገልግሎት (ለመዝሙር) ሰጥታ እንደነበር ይታወሳል።

ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት እንዲሁም የበርካታ የልጅ ልጆች አያት ነበረች።

ለቤተሰቦቿ፣ ለአድናቂዎቿና ለመላው የጥበብ አፍቃሪያን መጽናናትን እንመኛለን። ፈጣሪ ነፍሷን በገነት ያኑርልን!




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1