ለብዙዎች ጥላ ሆኗል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ጥር 15 ቀን 1976 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ምስረታው በህመሙ ለተጠቁ ወገኖች መረጃ የሚሰጥበትንና ሕክምና የሚሻሻልበትን መንገድ ለመወያየት ምቹ መድረክ ለመፍጠር ያለመ ነው።

ማህበሩ የተቋቋመው በኢትዮጵያ ህክምና ማህበር፣ በጤና ባለሙያዎች እና በስኳር ህሙማን በጎ ፈቃደኞች ጥረት ሲሆን በሀገሪቱ ይህም የመጀመሪያው በሕሙማን የተመሰረተ ማህበር ያደርገዋል።

አብዛኛዎቹ የስኳር ህሙማን በቤታቸው የመመርመር አቅም ስለሌላቸው ምስጋና ለዚህ በጎ ሃሳብ ጀማሪዎች ይሁንና በርካታ አባላትቱ ወደ ዋናው ማዕከል መጥተው አገልግሎት ያገኛሉ።

ማህበሩ 1994 ዓ.ም ነፃውን የስኳር መጠን ምርመራ የጀመረ ሲሆን አገልግሎቱንም እስከ መጋቢት 1997 ዓ.ም ድረስ ቀጥሏል።

ከዚያ ጊዜ ወዲህ ግን በሕክምና ግብዓቶች እጥረት በተለይም የመመርመሪያ ስትሪፖች እጥረት ምክንያት አገልግሎቱን በጣም በትንሽ ክፍያ ብቻ በመስጠት ላይ ይገኛል።

ማህበሩ በጥቂት ሰዎች የተጀመረ ትንሽ ዘር ቢሆንም ዛሬ ላይ ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ደዌ፣ የስኳርና ሆርሞን ሕክምና ስፔሻሊስት እና የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጌታሁን ታረቀ እንዳስታወቁት ​ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሕክምናውን የማሻሻል፣ የፖሊሲና የሕክምና ጋይድላይን ስራዎችን የመስራት እንዲሁም የክህሎት ማሳደጊያ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በተለይም ባለፉት 14 ዓመታት ከ20 ሺህ በላይ ለሆኑ የዓይነት አንድ ስኳር ሕሙማን በነጻ የኢንሱሊን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 17 ሺህ 500 ታካሚዎችን በተሻሻሉ አዳዲስ የኢንሱሊን ዓይነቶችና በግሉኮሜትር መመርመሪያዎች በነጻ እየረዳ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም ማህበሩ የስኳር ሕመም ዋነኛ ተጽዕኖ የሚታይበትን የአይን ሕመም ቀድመው የሚያውቁ ዘመናዊ ማሽኖችን ለጥቁር አንበሳና ለጎንደር ሆስፒታሎች ያቀረበ ሲሆን፣ አሁንም ለአይደር ሆስፒታል ተመሳሳይ መሳሪያ የማስረከብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ቀደም ብለን እንደዘገብነው ማህበሩ ከዳሬክት ሪሊፍ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የመድኃኒት ማቀዝቀዣዎች ለጤና ሚኒስቴር አበርክቷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: