ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በምስራቅ በለሳ ውስጥ የሚገኘውን የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳምን ጎበኙ!
ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በማዕከላዊ ጎንደር በምስራቅ በለሳ በሚገኘው በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በገዳማውያኑ እየተሠሩ ያሉትን የልማት ሥራዎችም ጉብኝት አድርገዋል።
ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው፣ በመሠራት ላይ ያለውን የአብነት ትምሕርት ቤት፣የዘመናዊ ትምሕርት ቤት እና ሌሎችንም የልማት ስራዎች የጎበኙ ሲሆን “ከቃል በላይ ነው የተሠራው፥ በዐይናችን ያየነውን ነገር ለመመስከር የአባቶችና እናቶች ሥራ ያስገድደናል” ብለዋል። የጀመርነውን ድንቅ ስራ ከፍጻሜ ለማድረስም አሁንም እንተባበር” ሲሉም መልእክታቸውን አሰምተዋል።
የብፁዕ አባታችን ቡራኬ ከሁላችንም ጋር ይሁን!
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444



Source: GetuTemesgen








No comments yet.