የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል ገንዘቦች እና በቨርቹዋል ሀብቶች ዝውውር ላይ ጥብቅ እገዳ ጣለ​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል ገንዘቦች እና በቨርቹዋል ሀብቶች ዝውውር ላይ ጥብቅ እገዳ ጣለ
​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህግ ከተፈቀደው ውጪ በማናቸውም የቨርቹዋል ሀብቶች ግብይት ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።
​እገዳው ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ለማንኛውም ክፍያና ኢንቨስትመንት የሚያገለግሉ በዲጂታል መልኩ የሚተላለፉ መግለጫዎችንም ያካትታል።
​በተለይም የሚከተሉት ተግባራት ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው ብሏል ባንኩ;
👉በቨርቹዋል ሀብት እና በመደበኛ ገንዘብ መካከል የሚደረግ መመንዘር
👉​በቨርቹዋል ሀብቶች መካከል የሚደረግ ልውውጥና ዝውውር
👉​የቨርቹዋል ሀብቶችን ማስቀመጥ፣ ማስተዳደር እና የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት
​ህብረተሰቡ ከህጋዊ ተጠያቂነት፣ ከማጭበርበር፣ ከሳይበር ጥቃት እና ከከባድ የገንዘብ ኪሳራ ለመጠበቅ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ባንኩ አሳስቧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1