*ከጎዳና ህይወት እስከ አለም አቀፍ መድረክ
*አስከፊ ከሆነ የጎዳና ህይወት ተነስተው ከዝነኛዋ ሻኪራ ጋር እስከ መጣመር የደረሱት ጥቋቁር የአፍሪካ ወርቆች
#Ethiopia | በምስራቅ አፍሪካ የጥበብ ዓለም ውስጥ የብዙዎችን ቀልብ የሳቡት የኡጋንዳው የዳንስ ቡድን ጌቶ ኪድስ የችሎታ እና የጽናት ተምሳሌት በመሆን ዓለምን እያስደነቁ ይገኛሉ።
ቡድኑ የተመሰረተው በኡጋንዳዋ ካምፓላ ከተማ በሚገኘው የካታዌ (Katwe) ሰፈር ነው።
በዳውዳ ካቫማ አማካኝነት የተደራጁት እነዚህ ታዳጊዎች መነሻቸው ከምንም ነበር ማለት ይቻላል።
እነዚህ ህጻናት በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የነበሩ ከድህነት ጋር በጎዳና ህይወት ላይ የነበሩ ናቸው።
ይህ ብልሁ ዳውዳ ካቫማ የተባለው ወጣት ታዳጊዎችን በመሰብሰብ በሙዚቃ እና በዳንስ ተስፋ እንዲሰንቁ ብሎም ስማቸውን አለም እንዲያውቀው አድርጓል።
የዳውዳ ካቫማ አላማ የነበረው መዝናኛን ብቻ ሳይሆን ችሎታን በመጠቀም የጎዳና ላይ ህይወት በአማራጭ መንገድ ሊቀየር እንደሚችል ለዓለም ማሳየት ነበር።
ቡድኑ መጀመሪያ ላይ ትኩረት ያደረገው ጎዳና ላይ በመጨፈር የነበረ ሲሆን የነበራቸው ጉልበት እና ተፈጥሯዊ የዳንስ ችሎታ በየማህበራዊ ሚዲያው በወጡ አጫጭር ቪዲዮዎች የዓለምን ትኩረት በቶሎ እንዲስቡ አድርጓቸዋል።
ጌቶ ኪድስ ከኡጋንዳ አልፈው ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙት በተለያዩ የዓለም የሙዚቃ ቪዲዮዎች ላይ በመሳተፍ ነው።
በተለይም በፈረንጆቹ 2017 ላይ ከፈረንሳዊው አርቲስት ፍሬንች ሞንታና (French Montana) ጋር በሰሩት “Unforgettable” የሙዚቃ ቪዲዮ አማካኝነት ስማቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው ተሰማ።
ጌቶ ኪድስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በታላላቅ የሙዚቃ ሽልማቶች ላይ ተጋባዥ ሆነዋል።
በዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ በመቅረብ የኡጋንዳን እና የአፍሪካን ስም በከፍተኛ ደረጃ እያስጠሩም ይገኛሉ።
በቅርቡ በተጠናቀቀው የ2026 የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ከዝነኛዋ ሻኪራ ጋር በመጣመር ባሳዩት ብቃት የስኬት ጉዟቸውን ከፍታ ላይ አድርሰውታል።
ዛሬ “ጌቶ ኪድስ” የዳንስ ቡድን ብቻ ሳይሆን የበርካታ አፍሪካውያን ታዳጊዎች የህልም ምሳሌ ሆነዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#UgandaGhettoKids
#DancingwithShakira
#WorldCupfinal
Source: GetuTemesgen









No comments yet.