ሕፃናትን በማታለል የደፈሩ ጥበቃ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ ሶዶ በር ቀበሌ በሚገኘው የንጋት ትምህርት ቤት ጥበቃ ሆኖ የሚሠሩት ታዲዎስ ሞታ የተባለ ግለሰብ፣ የ5 እና 7 ዓመት ሕፃናት ላይ ግብረ-ሥጋ ድፍረት በመፈጸማቸው የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ተጣለባቸው።

ተከሳሹ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ሕፃናቱን “ዥዋዥዌ ትጫወታላችሁ” በማለት በማታለል በሚሠሩበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወደሚገኝ ማደሪያ ክፍል በማስገባት ወንጀሉን ፈጽመዋል።

ፖሊስ በሰበሰበው ማስረጃ ድርጊቱ መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል።

ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የቦዲቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 60/ሀ እና 627/1 መሠረት ጥፋተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን እንዲሁም መሰል ወንጀል ፈጻሚዎችን ለማስተማርና ለመከላከል በሚል የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ወስኖበባቸዋል።

የቦዲቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: