ዘማሪት ኢየሩሳሌም አየለ «የጄሪ ጩኮ»ን ጨምሮ ባህላዊ ምግቦችን ለኤክስፖርት አቀረበች!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I ታዋቂዋ ዘማሪ ኢየሩሳሌም አየለ (ጄሪ) የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችን(ጩኮ) እና የቅመማ ቅመም ምርቶችን ለውጭ ሀገር ገበያ (Export) ለማቅረብ ያዘጋጀችውን አዲስ የንግድ ስራ እና የምርት አይነቶች በይፋ አስተዋወቀች።

በእናትና አባቷ የሼፍነት ሙያ እና በቤተሰብ የሙያ ውርስ ላይ ተመስርቶ የተጀመረው ይህ የንግድ ስራ፤ በዋናነት «ጄሪ»በሚል የምርት ስም የሚታወቅ ሲሆን፣ የቦቆጂን የሳር እና የጦስኝ ለጋ ቅቤ በመጠቀም የተዘጋጀውን «የጄሪ ጩኮ» ጨምሮ አነባበሮ፣ በቅቤ የታሸገ ቆሎ፣ ዳጣ እና ሚጥሚጣን ለገበያ አቅርቧል።

ዘማሪ ኢየሩሳሌም እንደገለፀችው፣ ምርቶቹ ሙሉ በሙሉ በቤት ውስጥ በከፍተኛ ንፅህና እና ጥንቃቄ በራሳቸው እጅ የሚዘጋጁ መሆናቸዉን ገልፃለች።

ዘማሪ እየሩሳሌም አክላም ምርቶቹ አለም አቀፍ የኤክስፖርት መስፈርትን (Export Standard) አሟልተው የተሰሩ በመሆናቸው ቀዝቃዛ ቦታ ላይ በመጠበቅ ከ1 ወር እስከ 1 ዓመት ድረስ ሳይበላሹ መቆየት እንደሚችሉ ገልፃ በተለይም በቅቤ የታሸገው ቆሎ የምርቱን ትኩስነት እና ጥራት ለመጠበቅ ሲባል በልዩ ትዕዛዝ ብቻ የሚዘጋጅ መሆኑ ገልፃለች።

የምርቱ”ዋና አላማ ከሀገር ውስጥ አልፎ የኢትዮጵያን ባህላዊ ጣዕሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ ነው” ስትል የተናገረችው ዘማሪ ኢየሩሳሌም፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ካናዳ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ጀርመን ምርቶቹን ለመላክ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጻለች።

በአሁኑ ወቅት በቤተሰብ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ኢንተርፕራይዝ፣ ስራው ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ድካም የሚይዝ ቢሆንም ምርቶቹን ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መታቀዱ ተገልጿል።

በመጨረሻም ድርጅቱ ወደፊት አቅሙን በማስፋፋት ለበርካታ ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል የመፍጠር እና አዳዲስ ባህላዊ ምርቶችን ወደ ገበያ የማስገባት እቅድ እንዳለው ነዉ የተገለፀዉ።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: