አድማስ ዩኒቨርሲቲ ከ5,000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:-አድማስ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በርቀት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ መርሃ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ5,000 በላይ ተማሪዎች በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 73.16 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ ይህም ተቋሙ ለሴቶች የከፍተኛ ትምህርት ተሳትፎ እያደረገ ያለውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል።

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት አምባሳደር ዶ/ር የሺመብራት መርሻ ካሳ፣ የዩኒቨርሲቲው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ይብራህ ግርማይ፣ የሠኔት አባላት፣ መምህራንና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ተቋሙ ላለፉት 27 ዓመታት ከ100,000 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ለሀገር ልማት ማበቃቱን የገለፀ ሲሆን ከአንድ አነስተኛ የማሰልጠኛ ማዕከል የተነሳው አድማስ ዩኒቨርሲቲ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ 10 ካምፓሶችንና በርካታ የርቀት ማዕከላትን የከፈተ እና በሶማሊላንድና በፑንትላንድም ተመራጭ ተቋም ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ነዉ የተገለፀዉ።

አድማስ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ጥራትና በስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ምዘናዎች በርካታ አገር አቀፍ ዕውቅናዎችን ያገኘ ሲሆን፣ በቅርቡም በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የዳግም ምዝገባ መስፈርትን ካሟሉ ጥቂት የግል ተቋማት አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን ተቋሙ 18ኛውን ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በመጪው ጳጉሜ ወር እንደሚያካሂድ ተገልፆ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የነፃ ትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ለማህበረሰቡ መስጠቱ ተገልጿል።

በመጨረሻም፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ለመቀጠል ለሚፈልጉ ተመራቂዎች ለሚጠብቃቸው ሀገርአቀፍ የመግቢያ ፈተና ዩኒቨርሲቲው ነፃ የማጠናከሪያ ድጋፍ እንደሚሰጥ የገለጹት ፕሬዚደንቱ፣ ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው መልካም የምረቃ በዓል እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: