በክልሉ እናቶች ሥነ-ልቦናዊ ጫና እየደረሰባቸው በመሆኑም የፌደራል መንግሥት የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ እንዳለበት የትንሳዔ ስርዓት ቃንጫ ሗቂ ፓርቲ አስታውቋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ጎዶፋይ ይሄን ያሉት ከአሐዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት የትግራይ ሕዝብ እንጂ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
በክልሉ ያሉ የፓለቲካ ሀይሎች ሕዝቡንና ሰራዊቱን በመክፈል አለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
የክልሉ ሕዝብና እናቶች መንግሥት ይድረስልን በማለት ላቀረቡት ጥሪ የፌደራል መንግሥት አፋጣኝና አዎንታዊ ምላሽ መስጠት አለበት ሲሉ አንስተዋል።
የፌደራል መንግሥት ትግራይ ክልል በሚመለከት ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ብቻ ሳይሆን አካታች የሆነ ግንኙነት መፋጠር አለበት ብለዋል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ምሁራንን ፣የኅብረተሰብ ተወካዮችን ሰብስቦ የምክክር መድረክ ማዘጋጀት ይጠበቃልም ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል።
ከትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም እና ከሕግ ማስከበር ሥራዎች ጋር በተያያዘ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡ የተለያዩ አስተያየቶችን መንግሥት በማጤን መፍትሔ መስጠት እንዳለበት ጠቁመዋል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.