ባደኩበት ሰፈር፤ በተሻለ ኑሮ!

- Advertisement -
Sidebar AD

አባይ ሆምስ በንጉሶቹ መንደር Kings Residence የተባለውን ፕሮጀክቱን በይፋ ሊያስጀምር ነው።
አባይ ሆምስ ሪል እስቴት በጎተራ ቄራ አካባቢ የሚገነባውን ፕሮጀክቱን ሀምሌ 25፣ 2018 ዓ.ም. በይፋ ያስጀምራል።
ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በርካታ ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም፣ በመጠገን፣ በማስመጣት እና በመሸጥ የሚታወቀው አባይ የቴክኒክ እና ንግድ አ.ማ. ላለፉት ሶስት ዓመታት አባይ ሆምስ በሚል የንግድ ስያሜ ወደ ሪል እስቴት ልማት በመግባት ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ፊት ለፊት በሚገኘው ይዞታው ላይ 3B+G+25 የሆነ ግዙፍ እና በርካታ አገልግሎቶችን የያዘ ቅይጥ የንግድ እና የመኖሪያ ህንፃ መገንባት የጀመረ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በጎተራ/ቄራ ሁለተኛው የሆነውን Kings Residence የተባለውን ፕሮጀክቱን ሀምሌ 25፣ 2018 ዓ.ም. በይፋ ሊያስጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ ፕሮጀክት 668 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡም ምቹ እና በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ፣ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻርጅ ማድረጊያ፣ የከርሰ ምድር ውሃ፣ የጋራ መዝናኛ ስፍራን ፣ ጂምናዚየም፣ 3 የመኪና አሳንሰሮችን ያካተተ ምቹ የመኖሪያ ስፍራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ አገልግሎት ብቻ የሚውል ሲሆን የግንባታው ፕሮጀክት አጠቃላይ ተሰርቶ ሲያልቅ 89 አፓርትመንቶችን የሚይዝ እና በወለልም 5 አፓርትመንቶች ብቻ የሚኖሩት ይሆናል ተብሏል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: