#Ethiopia | ህንድ ተማሪዎች ያስነሱትን ተቃውሞ ለመበተን መሳርያ ተጠቅሟል የተባለው የፖሊስ አባል ከስራ አግዳለች።
ከሰሞኑ በህንድ ከፈተና ስርቆት ጋር በተያያዘ የተነሳውን የተማሪዎች ተቃውሞ ለመበተን በሚደረገው ጥረት ወቅት Ak 47 የተሰኘው የጦር መሣሪያ ወደ ተማሪዎች ተኩሷል የተባለው የፖሊስ አባል ከሥራ መታገዱ አልጀዚራ ዘግቧል።
ተቃውሞው የተቀሰቀሰው በፈተና ስርቆትና ማጭበርበር ምክንያት ሲሆን የሕዝቡን ቁጣና የተማሪዎችን ተቃውሞ ተከተሎ የህንድ የትምህርት ሚኒስትር ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ መገደዳቸው ይታወሳል።
በቪዲዮ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ ከፍተኛ ቅሬታን ያስነሳው የፖሊስ አባሉ ድርጊት መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ ያልተመጣጠነ እና ከመጠን በላይ የሆነ የኃይል እርምጃ ተጠቅሟል የሚል ጥሰት እና ውግዘት አስከትሎበታል።
ድርጊቱ የፖሊስ ሥነ ምግባርንና የሕግ ማስከበር ደንብን የጣሰ በመሆኑ በፖሊስ አባሉ ላይ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ታውቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#India #police #Students #demonstration
Source: GetuTemesgen









No comments yet.