ሪያል ማድሪድ ለቪኒሲየስ 160 ሚሊዮን ዩሮ ጠየቀ አርሰናል ሂሳቡን ለመክፈል ፍላጎት ማሳየቱ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

የብራዚሉንና የሪያል ማድሪዱን የፊት መስመር ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለማስፈረም ሰፊ ፍላጎት ያሳየው አርሰናል፣ ማድሪዶች ለተጫዋቹ የጠየቁትን ግዙፍ የዝውውር ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑ ተዘገበ።

ሪያል ማድሪድ የ26 ዓመቱን አጥቂ የዝውውር ዋጋ 160 ሚሊዮን ዩሮ (137 ሚሊዮን ፓውንድ)ማድረጉን የስፓንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የክለቡ ፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ከተጠቀሰው ዋጋ በታች ለማንኛውም ድርድር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የዝውውር ፓኬጁ የተረጋገጠ ክፍያ እና ከተጫዋቹ ብቃት ጋር የተያያዙ ተጨማሪ ክፍያዎችን (add-ons) ያካተተ ነው።

እንደ ቪኒሲየስ ያሉ በውል ማጠናቀቂያ ዓመታቸው ላይ የሚገኙ ልሂቃን አጥቂዎች የወደፊት ቆይታ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ቢሆንም፣ የሪያል ማድሪድና የአሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ዋና ፍላጎት ተጫዋቹን አዲስ ውል ማስፈረም ነው።

ማድሪዶች በዚህ ሳምንት ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ተጨማሪ ድርድር ለማድረግ ቀጠሮ የያዙ ሲሆን፣ ተጫዋቹን በነጻ ከማጣት ይልቅ አሁን ለመሸጥ ከተገደዱ ግን የተመነውን ከፍተኛ የካሳ ክፍያ ቅድመ ሁኔታ አድርገዋል።

ባለፈው የውድድር ዘመን ለማድሪድ 22 ግቦችን ማስቆጠር የቻለውና በዓለም ዋንጫው ደግሞ ለብራዚል 4 ግቦችን ያስቆጠረው ቪኒሲየስ፣ አሁንም የአርሰናል ዋነኛ የዝውውር ኢላማ ነው። ምንም እንኳን በሁለቱ ክለቦች መካከል ይፋዊ የጽሁፍ ድርድር ባይጀመርም አርሰናል የፊት መስመሩን በጥራት ለማጠናከር ሲል ማድሪድ የጠየቀውን ግዙፍ የዝውውር ሂሳብ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆኑ ተሰምቷል።

በሪያል ማድሪድ በኩል የሚደረገው የአዲስ ውል ድርድር ካተቋረጠ በቀር አርሰናል የተመነውን ዋጋ በመክፈል ኮከቡን ወደ ኤሚሬትስ ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2