ኢራን ላይ የተደረገው ጦርነት አሜሪካን እንዳዳከማት አንድ ባለስልጣን ተናገሩ
የአሜሪካው ኮንግረስ አባል ቶማስ ማሲ፣ የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ባካሄደው ጦርነት የአገሪቱን መረጋጋት እና ሀብት በእጅጉ ጎድቷል ሲሉ ከሰዋል። “አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት ምክንያት በእጅጉ ተዳክማለች” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
“ይህ አስተዳደር የሚሳኤል መከላከያ አቅማችንን አሟጧል፣ የነዳጅ ክምችታችንን ጨርሷል፣ ወታደሮቻችንን መስዋዕት አድርጓል፣ የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ እንዲንር አድርጓል፣ ዕዳችንን ጨምሯል እንዲሁም የአገር ውስጥ ፍላጎቶቻችንን ችላ ብሏል ፤ ይህ ሁሉ ደግሞ ለእስራኤል ሲባል ነው” ሲሉም አክለው ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ በተካሄደው ጦርነት የጦር መሳሪያዎች ክምችት እየቀነሰ መምጣቱን የሚገልጹ ሪፖርቶችን ውድቅ አድርገዋል፣ ለዎል ስትሪት ጆርናል እንደተናገሩት የአገሪቱ የጦር መሳሪያዎች አቅርቦት ከፍላጎታችን አንፃር እጅግ የላቀ ነው ሲሉ ትችቱን አስተባብለዋል። አሜሪካም ሆነ ኢራን ለሁለተኛ ቀን ወታደራዊ ጥቃቶችን በማቆማቸው የዲፕሎማሲ ተስፋዎች ብቅ ብለዋል።
አሜሪካ በኢራን ላይ የሁለት ሳምንት የቦምብ ጥቃት ዘመቻዋን ካቆመች በኋላ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከ5 በመቶ በላይ ቀንሷል፣ ይህም ወደ ዲፕሎማሲያዊ ሽግግር ሊያመራ እንደሚችል ያሳያል። በሌላ በኩል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በካስፒያን ባህር ውስጥ በሚገኝ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት በተመለከተ የአፀፋ ምላሽ ሳይሰጠው አይተውም ያሉ ሲሆን አንድ የመርከብ አባልን ለገደለው ጥቃት ዩክሬን ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.