የዜሮ እዳ ባለቤቶች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) በኩል የሚሰጡ የብድር አቅርቦት እና የፋይናንስ ድጋፍ ለብዙ አፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው።

2026 ከተቋሙ አነስተኛ የብድር እዳ ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ወቅታዊ መረጃ አነስተኛ የብድር እዳ ካለባቸው ሀገራት መካከል በመጀመሪያው ተሰልፈው የሚገኙት በድርጅቱ አሰራርና አጠራር መሠረት የዜሮ እዳ ባለቤት የሆኑት ሀገራት ናቸው።

በዚህም ቦትስዋና፣ ሊቢያ፣ ኤርትራ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ እና ሞሪሸስ ከIMF ጋር አሁናዊ የብድር እዳ የሌለባቸው ሀገራት በመሆን የዝርዝሩን አናት ይዘዋል።

በሌላ በኩል ከተቋሙ ጋር ንቁ የብድር ፕሮግራም እያካሄዱ ነገር ግን በዝቅተኛ የብድር መጠን ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት 10 የአፍሪካ ሀገራትም አሉ።

ሌሶቶ፣ ኤስዋቲኒ፣ ጂቡቲ፣ ኮምሮስ፣
ሳኦ ቶሜ ፕሬንስፔ፣ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ጊኒ ቢሳዎ፣ኬፕ ቨርዴ፣ ሲሸልስ እና ቡሩንዲ ከድርጅቱ አነስተኛ የብድር መጠን ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ተብሏል።

አነስተኛ የብድር እዳ ካለባቸው ሀገራት መሀከል አብዛኞቹ ደሴትና አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ናቸው።

የIMF እዳ አነስተኛ መሆኑ ሀገራቱ የራሳቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በነጻነት ለመቅረጽና ከውጭ ጫና ለመጠበቅ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላቸው ነው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚናገሩት።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#IMF #debt #Economi


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2