የቀድሞ የሲዳማ ክልል የፀጥታ አመራሮች በጽኑ እስራት ተቀጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ በ10 ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራት፣ የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ደግሞ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ውሳኔ አስተላለፈ።

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ባዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ፣ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ከሳሽነት የተመሰረተባቸውን ክስ መነሻ በማድረግ የቀረቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መመዘኑን ገልጻል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ስልጣናቸውን አላግባብ በመገልገል “የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት (ሲነሠ)” የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀትና ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸም ጥፋተኛ ሆነው አግኝቷቸዋል።

በዚህም መሰረት አንደኛ ተከሳሽ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ በ10 ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራት እና በ4,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል። ሁለተኛ ተከሳሽ የቀድሞው የፖሊስ ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ በበኩላቸው በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እና በ1,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2