አድማስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን ከ5,000 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አድማስ ዩኒቨርስቲ በመደበኛና በርቀት ትምህርት፣ በድህረ ምረቃ ፣ በድግሪ፣ በዲፕሎማና በሰርተፊኬት ያስተማራቸውን ከ5,000 በላይ ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

ዩኒቨርስቲው ላለፋት 27 ዓመታት በመደበኛና በርቀት ትምህርት፣ በድግሪ፣ በዲፕሎማና በሰርተፊኬት በርካታ ተማሪዎችን አስመርቆ፣ በሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ የሚፈለገውን የተማረ የሰው ሀይል አሰልጥኖ በማቅረብ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዳበረከተ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሞላ ፀጋይ የገለፁ ሲሆን የትናንቱን የቴክኒክና ሞያ ተመራቂዎችን ጨምሮ ከ5000 በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁን ከእነዚህም ውስጥ ከ73.16 ፐርሰንቱ በላይ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሞላ አክለውም ዩኒቨርስቲው ከዚህ በፊት የርቀት ትምህርት በመንግስትም ሆነ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳይሰጥ ለሶስት ዓመታት ከተከለከለ በኃላ እንደገና ተፈትሾ፣ ጥራታቸው ተረጋግጦ በርቀት ትምህርት እንዲያሰለጥኑ ከተፈቀደላቸው ግንባር ቀደም ተቋማት አድማስ አንዱ ነው መሆኑንና ከዚህ በፊት፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ ባደረገው የተቋሟት የጥራት ደረጃ ምደባ መሠረት ከ 85% በላይ ውጤት አስመዝግበው የመጀመሪያው ረድፍ ከተቀመጡት ሦስት ተቋማት ውስጥ ዩኒቨርሲቲው አንዱ ነው ብለዋል፡፡

ባሳለፍነው 2017 ዓመትም የአዲስ አበባ የሥራና ክህሎት ቢሮ በዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ነበራቸው ካላቸው 13 ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ዩኒቨርሲቲውን በአንደኛ ደረጃ አስቀምጦታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው፣ ከመደበኛው የመማር ማስተማር ጎን ለጎን፣ አጫጭር ስልጠናዎችና የማማከር አገልግሎቶች በመስጠት፣ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ጥናትና ምርምሮች በማካሄድ ውጤቱን ለህብረተሰቡ በማሳወቅ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ሀገር አቀፍ የተማሪዎች የጥናት እና ምርምር ሲምፓዚየምን እስከ አሁን ለሰባተኛ ጊዜ አካሂዷል፡፡

ከአንዲት ስልጠና የምታካሂድ ቦታ ተነስቶ ባለ 10 ካምፓሶችና የበርካታ የርቀት መስጫ ማዕከላት ባለቤት የሆነው አድማስ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ወጥቶ በሶማሊላንድና በፑትላንድም ዩኒቨርስቲ ከፍቷል፡፡

በዚህ ትናንትና ዛሬ በተካሄደው የምረቃ ስነስርዓት ላይ የቀድሞ የትምህርት ሚኒስቴር አምባሳደር ገነት ዘውዴ፣ክብርት አምባሳደር ዶ/ር የሺመብራት መርሻ ካሳ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ይብራህ ግርማይን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2