የቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የቀድሞው የፖሊስ ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጽኑ እስራት ውሳኔ ተላላፈባቸው።
የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ፍርድ ቤቱ በከሳሽነት የቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማመሳከር ተከሳሾቹ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጧል። ተከሳሾቹ ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም «የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት» (ሲነሠ) የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀት እና ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸማቸው ነው ጥፋተኛ የተባሉት።
በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፦
* 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እና በ4,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ፤
* 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሽመልስ ቶማስ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና በ1,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2