በ108 ዓመታቸው የመኪና መሪ አልለቅም ያሉት የእድሜ ባለፀጋዋ ሜሪ

- Advertisement -
Sidebar AD

መሪ በቀላሉ የምንደሰት ከሆነ የማይቻል ነገር የለም ይላሉ

#Ethiopia | በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ108 አመት ባለፀጋዋ መሪ በሰሞኑ የመንጃ ፍቃዳቸውን እስከ ፈረንጆቹ 2033 ድረስ አሳድሰዋል።

108 ዓመታቸው ላይ የሚገኙት መሪ በራሳቸው መኖሪያ ቤት ብቻቸው ከመኖራቸውም በላይ መኪናቸውንም እያሽከረከሩ ይገኛሉ።

ሜሪ ፍሊፕ የተባሉት እኚህ ባለታሪክ ለረጅም እድሜ የበቁበትና ጤናማ የሆኑበትን ምስጢር አካፍለዋል።

በቅርብ ጊዜ የመንጃ ፈቃዳቸውን እስከ ፈረንጆቹ 2033 ድረስ ያደሱት ሜሪ ሙሉ በሙሉ ነፃነታቸውን ጠብቀው በራሳቸው መኖር እንደሚወዱ ይናገራሉ።

ራሴን ሙሉ በሙሉ በራሴ ነው የምንከባከበው የሚሉት ሜሪ በየቀኑ ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን መስራት እንደሚያዘወትሩ ይናገራሉ።

ሜሪ እረጅም ዕድሜ የመኖራቸው ምክንያት ሲናገሩ በሕይወታችን ውስጥ ከባድ ችግሮች ሲገጥሙን አዎንታዊ ጎኑን ማየትና ሁልጊዜም ፈገግታን ማብዛት ጤናማ ህይወት መኖር ይቻላል ብለዋል።

በሰው ላይ አለመደገፍ እና የራስን የቤት ውስጥ ስራዎች በተቻለ መጠን በራስ መወጣት ያስፈልጋልም ሲሉ ተናግረዋል።

በቀላሉ ልንደሰትባቸው በሚያስችሉን አነስተኛ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እና ጭንቀትን ማስወገድ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#centenarian
#Drives #longlife
#Merryfelipe


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2