የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሰኔ 30 በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 9 ሺህ 558 ፍቺ መመዝገቡን አስታውቋል፡፡
ኤጀንሲው ይህንን የገለፀው የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግልጫ ነው፡፡
በመግለጫው ወቅት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ በአምስቱ የኩነት የምዝገባ ዓይነቶች ማለትም፡- ልደት፣ ሞት፣ ፍቺ፣ ጋብቻ፣ ጉዲፈቻ 500 ሺህ 363 ምዝገባዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በ2018 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 30 ድረስ 37ሺህ 149 የጋብቻ ምዝገባ ተከናውኗል ተብሏል፡፡
1 ሚሊዮን 500 ሺህ ተገልጋዮች በኤጀንሲው በኩል አገልግሎት ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ 2 ሚሊዮን 400 ሺህ አገልግሎቶች እንደተሰጡ አብራርተዋል።
ኤጀንሲው ይህን አገልግሎት ሲሰጥ በአንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን ሳይሆን በጤና ተቋማት እና በሌሎችም ተቋማት በመንቀሳቀስ ጭምር እንደሆነ አስረድተዋል።
በተለይ ከተማዋ ላይ በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ የአንድ መስኮት የአገልግሎት መስጫ በመክፈት የልደት እና የሞት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላይም የአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ በመክፈት በ11 የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ላይ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በተመስገን ተጋፋው
Source: Yeneta Tube









No comments yet.