#Ethiopia | በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ባለሀብቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝና በአሁኑ ወቅት አህጉሪቱ የ25 ቢሊየነሮች(በዶላር) እና ከ120 ሺህ በላይ ሚሊየነሮች(በዶላር) መኖሪያ መሆኗን የ«Henley & Partners» እና «New World Wealth» የሀብት ሪፖርት አመለከተ።
በወጣው አህጉራዊ መረጃ መሠረት ደቡብ አፍሪካ 41 ሺህ 100 ሚሊየነሮች በማፍራት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን፣ ግብፅ በ14 ሺህ 800 እንዲሁም ሞሮኮ በ7 ሺህ 500 ሚሊየነሮች ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ናይጄሪያ በ7 ሺህ 200፣ ኬንያ በ6 ሺህ 800፣ ሞሪሸስ በ4 ሺህ 800፣ አልጄሪያ በ2 ሺህ 700፣ ጋና በ2 ሺህ 600 እና ናሚቢያ በ2 ሺህ 500 ሚሊየነሮች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
ኢትዮጵያ ደግሞ 2 ሺህ 400 የዶላር ሚሊየነሮችን በማፍራት ከአፍሪካ በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.