ዘንድሮ ከ9 ሺህ በላይ ፍቺዎች ተመዝግበዋል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ 9,558 የፍቺ ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስታወቀ።

ይህንን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ ገልጸዋል።

በሪፖርቱ መሠረት፣ በበጀት ዓመቱ በአምስቱ የኩነት ምዝገባ ዓይነቶች (ልደት፣ ሞት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ጉዲፈቻ) በድምሩ 500,363 ምዝገባዎች ተከናውነዋል።

በተመሳሳይ 37,149 የጋብቻ ምዝገባዎችም ተመዝግበዋል።

ኤጀንሲው በዓመቱ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተገልጋዮችን በማስተናገድ 2.4 ሚሊዮን የሚጠጉ አገልግሎቶችን እንደሰጠ ገልጿል።

እንዲሁም በጤና ተቋማትና በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች 11 ቅርንጫፎች የአንድ መስኮት አገልግሎት በመክፈት የልደት፣ የሞት እና ሌሎች የሲቪል ምዝገባ አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረጉን አስታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#Ethiopia #AddisAbaba #CivilRegistration #Marriage #Divorce #News


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1