*ከሞት የተረፍኩት በገንዘቤ ሳይሆን ሰዎች ባስተላለፉብኝ መልካምነት ነው ይላል ዛካሪያ
#Ethiopia | ዛካሪያ ይባላል ተወልዶ ያደገው በካናዳ ኦናታሪዮ ነው።
ዛካሪያ የህክምና ትምህርት ዘርፍ ተመርቋል።
ጎዳና ላይ እየተዟዟረ ሰዎችን በመርዳትና መልካምነትን በማስየት በሚሰራቸው አነቃቂ ቪዲዮዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል።
በህይወቱ ውስጥ ከባድ የድብርት እና የብቸኝነት ጊዜያትን አሳልፏል።
በዚያ ፈታኝ ወቅት ያጋጠመውን የስነ-ልቦና ስቃይ ወደ አዎንታዊ ኃይል በመቀየር ማንም ሰው ብቻውን እንደሆነ እና ተረስቻለሁ ብሎ ማሰብ የለበትም” በሚል እምነት የሰዎችን ህይወት ማቃለልና መርዳት ጀመረ።
የዛካሪያ ቪዲዮዎች ልዩ የሚያደርጋቸው አስቀድሞ “እርዳታ የሚፈልግ ሰው” መስሎ የሚቀርብበት መንገድ ነው፡
መንገድ ላይ ያሉ ሰዎችን ወይም ነጋዴዎችን ተጠግቶ ትንሽ የኪስ ገንዘብ አጠረኝ ልትረዱኝ ትችላላችሁ እያለ ይጠይቃቸዋል።
አንዳንዴም በጣም ተጨንቂያለሁ ልታቅፉኝ ትችላላችሁ በሚልም ይጠይቃል።
በጥቂት ነገር እንኳን ሊረዱት ፈቃደኛ የሆኑትን ደግ ልብ ያላቸውን አዛውንቶች የጎዳና ተዳዳሪዎችን ወይም ተራ ሰዎችን ወዲያውኑ መልሶ በእጥፍ ይሸልማቸዋል።
ብዙዎች ከ1,000 ዶላር እስከ 1ሚሊዮን ዶላር ድረስ ይሸልማቸዋል።
ገንዘብ መስጠት ብቻ ሳይሆን ተቀምጦ የህይወት ታሪካቸውንና የሚያጋጥማቸውን ፈተና በቁጭትና በጽኑ ርህራሄ ያዳምጣል።
ዛካሪያ አነስተኛ ስጦታዎችን በመስጠት ብቻ አይወሰንም በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለምሳሌ ቤት የሌላቸው እናቶች የህክምና ክፍያ ያጠራቸው ሰዎችን ታሪክ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በማጋራት ከተከታዮቹ ሚሊዮን ዶላሮችን በማሰባሰብ ድንገቴ ፈንጠዝያ ይፍጥርባቸዋል።
በ TikTok፣ YouTube እና Instagram ላይ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች አሉት።
ሰዎች የእሱን ቪዲዮዎች የሚወዱበት ዋና ምክንያት በአሁኑ ዘመን በዲጂታል አለም አዎንታዊነትን ተስፋን እና የእውነተኛ ሰብአዊ ርህራሄን ምስል በግልጽ ስለሚያሳይ ነው።
ዛካሪያ መልካምነት ተላላፊ ነው ቁሳዊ ነገር ሳይሆን ሰብአዊነት ሰዎችን ከሞት ይታደጋል የሚል አስተሳሰብ ነው እኔን የሚገዛኝ ብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#canada
#ZacheryDereniowski
#MDMotivator
Source: GetuTemesgen








No comments yet.