ሳዳም በስቅላት!

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች አልተገኙም!

#Ethiopia | ​እ.ኤ.አ. መጋቢት 20 ቀን 2003 አሜሪካ ከብሪታንያ እና ከሌሎች አጋሮቿ ጋር በመሆን በኢራቅ ላይ ድንገተኛ ወረራ ፈጸመች።

የወረራው ዋነኛ ምክንያት ሳዳም ሁሴን የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች ባለቤት ናቸው ለዓለምም ስጋት ደቅነዋል የሚል ነበረ።

ይህንን ተከትሎ በባግዳድ ሰማይ ስር የተካሄደው ከባድ የቦምብ ድብደባ የብዙ ንጹሃንን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን መኖሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል።

በርካታ ቤተሰቦች ሲፈናቀሉ፣ ሕፃናት ተቀብረዋል አገሪቱም እስከዛሬ ድረስ ወደማያበቃ መከራና ውዥንብር ውስጥ ገብታለች።

​ከወራት መሸሸግ በኋላ በታህሳስ 13 ቀን 2003 ሳዳም ሁሴን በተክሪት አቅራቢያ በአሜሪካ ጦር ከተያዙ በኋላ በጥቅምት 19 ቀን 2005 በባግዳድ በከፍተኛ ጥበቃ ሥር በሚገኘው የኢራቅ ከፍተኛ ችሎት ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በሕዳር 5 ቀን 2006 በ1982 በዱጃይል ከተፈጸመው የሰዎች ግድያ ጋር ተያይዞ በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በሞት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ሲሆን፣ በታህሳስ 30 ቀን 2006 ቅጣታቸው ስቅላት ሆኗል።

ሆኖም ለወረራውና ለተከተለው የሃያ ዓመታት መከራ መነሻ የተደረጉት የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች በኢራቅ ምድር በጭራሽ ሳይገኙ ቀርተዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1