በቴሌብር ዲጂታል ብድር ውዝፍ ዕዳ ያለባቸው ተበዳሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እና ክስ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ዳሸን ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር መተግበሪያ አማካኝነት የወሰዱትን የዲጂታል ፋይናንሲንግ ብድር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባልከፈሉ ተበዳሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን እና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ክስ እየመሰረቱ እንደሚገኙ ይፋ አደረጉ።

​እ.ኤ.አ. ጁላይ 29 ቀን 2026 የወጣው የባንኩ መግለጫ እንደሚያመለክተው፡ ተበዳሪዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፡ ከዚህ ቀደም የተደረገውን የቅጣት ክፍያ ምሕረት ተጠቅመው ዕዳቸውን ያልከፈሉ ወገኖች ላይ የህግ አካሄድ ተጀምሯል። አስቀድመው ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ያልሰጡ ተበዳሪዎች ላይ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶ ከዋናው ዕዳ በተጨማሪ ባንኩ ለክስ ያወጣቸውን ልዩ ልዩ ወጪዎች እንዲሸፍኑ ውሳኔ እየተሰጠ ይገኛል።

​ዳሸን ባንክ አክሲዮን ማህበር የህዝብ ገንዘብ ለማስመለስ የጀመረውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፡ እስካሁን የክስ መጥሪያ ያልደረሳቸው ተበዳሪዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት እና ተጨማሪ አላስፈላጊ እንግልት እንዲሁም ወጪ ሳይደርስባቸው ያለባቸውን ዕዳ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: