ብቸኝነት ያለባቸው ሰዎች ለከባድ የልብ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸው በ19 በመቶ እንደሚጨምር በአዲስ ጥናት ተመላከተ
ብቸኝነት የአእምሮ ጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የልብን መዋቅር በቀጥታ በመጉዳት ለከፋ የጤና ችግር የሚያጋልጥ አሳሳቢ ችግር መሆኑን በአሜሪካ የልብ ማህበር (AHA) ይፋ የተደረገ አንድ አዲስ ጥናት አመላክቷል።
ጥናቱ እንዳመለከተው፣ ብቸኝነት የሰውነትን የጭንቀት መጠንን በመጨመር የጭንቀት ሆርሞኖች (እንደ ኮርቲሶል ያሉ) በሰውነታችን ውስጥ እንዲጨምሩ ያደርጋል።
ይህ ከብቸኝነት የሚመነጭ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጭንቀት ደግሞ፣ በጊዜ ሂደት የልብ ቫልቭን (Heart Valve) በመጉዳት ለከፋ የልብ ጤና መቃወስ እንደሚያጋልጥ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የተመራው ይህ የጥናት ቡድንአረጋግጧል።
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ክሪስታል ዋይሊ ሴኔ እንዳሉት፤ “የህክምና ባለሙያዎች ታካሚዎቻቸውን ስለ ማህበራዊ ግንኙነቶቻቸው ሊጠይቋቸው ይገባል፤ ይህን አለማድረግ ታካሚዎችን ለከፋ የልብ ጤና እክል አልፎ ተርፎም ለሞት ሊያጋልጣቸው ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በተጨማሪም ብቸኛ የሆኑ ሰዎች ሲጋራ ማጨስን፣ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣትን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግን የመሳሰሉ ጤናማ ያልሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎችን በብዛት ስለሚከተሉ፣ ይህ ልምምድ ለልብ እና የደም ስር ጉዳት መፋጠን ተጨማሪ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል።
የአሜሪካ ዋና የቀዶ ጥገና ሀኪም በፈረጆቹ 2023 ብቸኝነትን “የህዝብ ጤና ወረርሽኝ” ሲሉ ያወጁት ሲሆን፤ ችግሩ ያለዕድሜ የመሞት አደጋን በ26 በመቶ ከፍ እንደሚያደርገውና ይህም በቀን 15 ሲጋራዎችን ከማጨስ ጋር እኩል የሚመዘን ጉዳት እንዳለው መግለጻቸው ይታወሳል።
ይህ የችግሩ አሳሳቢነት የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከአንድ ዓመት በፊት ካወጣው ሪፖርት ያስታወቀ ሲሆን ፣ ድርጅቱ ብቸኝነትን በየዓመቱ ከ871ሺህ በላይ ሰዎችን ያለዕድሜ የሚቀጥፍ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት አድርጎ ፈርጆታል።
በተጨማሪም፤ ከልብ በሽታ፣ ስትሮክ እና ድብርት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ይህ አሳሳቢ ችግር በየሰዓቱ 100 ሰዎችን ለሞት እንደሚዳርግ መግለጹ አይዘነጋም።
በመሆኑም የህክምና ባለሙያዎች ‘የብቸኝነት’ እንደ አእምሮ ጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የልብ እና የደም ስር የጤና ስጋት በመሆኑ ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በጥናቱ አጽኖት ተሰጥቷል።
@Seledadotio

No comments yet.