አፍሪካ በየዓመቱ በታክስ ማጭበርበር ከ88 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አፍሪካ በየዓመቱ በሕገ ወጥ የታክስ ማጭበርበር ምክንያት ከ88.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምትጣ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ገለጹ።

የምዕራብ አፍሪካ የታክስ አስተዳደር ባወጣው መረጃ መሰረት ከአህጉሪቱ በሕገ ወጥ መንገድ ከሚሰወረው ታክስ መካከል 65 በመቶ የሚሆነው ግዙፍ ኩባንያዎች በደረሰኝ አማካኝነት የሚሰውሩት ሀብት ነው ብሏል።

በአህጉሪቱ የሚገኙ ግዙፍ የንግድ ተቋማት የታክስ ስወራ የሚፈጽሙበት አንደኛው መንገድ ሀብታቸውን የትርፍ ታክስ ወደማይጠየቅባቸው ሀገራት በማሸሽ እንደሆነ ጠቅሷል።

በተለይም እንደ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አንጎላ እና ኮንጎ ያሉ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀጉ አገራት የዚህ የሀብት ምዝበራ ዋና ገፈት ቀማሾች መሆናቸው ተጠቅሷል።

ይህ ከአፍሪካ በየዓመቱ የሚሸሸው የገንዘብ መጠን አህጉሪቱ ከውጭ ከምታገኘው አጠቃላይ እርዳታ የሚበልጥ ነው ተብሏል።

በዚህም የአፍሪካ አገራት የትምህርት የጤና እና የመሠረተ ልማት ግንባታ ለማከናወን የሚያደርጉትን ጥረት አዳክሞባቸዋል ነው ያለው።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚሉት አፍሪካውያን የታክስ ሕጎቻቸውን ካላጣበቁ እና የዲጂታል ቁጥጥር ሥርዓቶችን ካልዘረጉ አህጉሪቱ የራሷን ሀብት ተቀምታ በውጭ እርዳታ ላይ ጥገኛ ሆና መቀጠሏ አይቀሬ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Africa #taxadministration
#Tax #netincome #revenue


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: